=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሸሪዓዊ እና ሱናዊ ብቸኝነት ፤ ከተንኮልና ከተንኮለኞች መራቅህ ፣ ከስራፈቶች ፣ ከቦዘኔዎች እና ከሁከት ፈጣሪዎች መገለልህ ስብስብ ማለት መቻልን ፣ የህሊና እረፍትን ፣ መረጋጋትንና ህሊናህ በጥበብ ፈርጦች እንዲዳብርና ዓይኖችህም በእውቀት አፀድ ላይ እንዲዘዋወሩ ይረዳሃል።
ከመልካም ስራዎችና ጌታን ከመታዘዝ ከሚያግዱ ነገሮች ሁሉ ተገልሎ ብቸኛ መሆን የልብ ሃኪሞች በተሞክሮ የደረሱበት ፍቱን ፈውስ ነው። እኔም ወደ እሱ አመላክትሃለው። ከተንኮል፤ ከውድቅ ሦራዎች እና አላስፈላጊ ስብስቦች መራቅ አእምሮን ያዳብራል ፣ የአሏህን ፍራቻንም ያመጣል ፣ አሏህን የማውሳትና የመዘከር ውዴታን ያስከትላል። ምስጉን ስብሰባዎችንና የተወደሱ ቅልቅሎች ሊባሉ የሚችሉት ለአምስቱ የሶላት ጊዜያት ፤ በጁምዓ ሶላት ፤ በዕውቀት መድረኮች እና በመልካም ስራዎች ላይ ለመተባበር የሚደረጉ መሰባሰቦች ሲሆኑ ፤ የስራፈቶች እና የዛዛታ አራማጆች ስብሰባዎችን ግን ተጠንቀቅ ሽሽም። በወንጀልህ አልቅስ ፣ ምላስህንም ቆጥብ ፣ ቤትህም ይስፋህ። አልባሌ ቅልቅሎች በነፍስ ላይ የሚካሄዱ ጦርኖቶች ናቸው። በነፍስህ ውስጥ የሰፈኑ የመረጋጋትና የሰላም ስሜቶች ላይ ጦርነት እንደመክፈት ነው። ምክንያቱም እነርሱ የአሉባልታ ነገስታት እና የወሬ ጀግኖች ናቸው። እንዲሁም በመከራ ፣ አደጋና ፈተና የሚያበስሩ መጥፎ የገድ መምህራን ናቸው። ሞት ሳይመጣብህም በቀን ሰባት ጊዜ የሞትክ ያህል እንዲሰማህ ለማድረግ ይጥራሉ።
-<({አል-ቁርአን 9:47})>-
«ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም።»
ስለዚህ ከአንተ የምፈልገው ብቸኛው ምኞቴ ሙሉ ትኩረትህን በራስህ ጉዳዮች ላይ እንድታደርግ ፣ ለመልካም ንግግር እና ተግባር ሲቀር ቤትህ ውስጥ እንድትሆን ነው።
የዚያኔ ቀልብህ ተመልሶልህ ታገኘዋለህ። ስለዚህ ጊዜህን ከጥፋት ጠብቀው። እድሜህንም ከመግደል ፣ ምላስህን ከሃሜት ፣ ልብህን ከጭንቀት ፣ ጆሮህን ከአፀያፊ ቃላት ፣ ነፍስህንም ከመጥፎ ጥርጣሬ ጠብቅ። እነዚህን የተገበረ እውነታውን ይረዳል። ነፍሱን በውድቅ ምግባሮች ጀርባ ላይ ላስጋለበ ሰው ፤ ከሥራፈቶቹም ጋር ጊዜውን ላሳለፈ...........ደህና ሁን በልልኝ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|